አልበም ፱

Album 9

የአድናቆት ፡ ቀን (Yeadnaqot Qen)

የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ለወደደን
የሚገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እውነቱን ፡ እንወቅ ፡ ጠንቅቀን
ጀብዱው ፡ ገድሉ ፡ የሚወራለት
ጭፍራ ፡ አለቃው ፡ የሚስግዱለት
እግዚአብሔር ፡ ምሥጉን ፡ ሥም ፡ ያለው
አድናቆቱም ፡ ምሥጋናውም ፡ መገረሙም ፡ ለእርሱ ፡ ሥም ፡ ነው
ማነው ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራ ፡ ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የቀየሰው
ማነው ፡ በአፍንጫው ፡ እፍ ፡ ያለ ፡ የሕይወትን ፡ እስትንፋስ ፡ ለሰው
ማነው ፡ ነፋስን ፡ አንፋሹ ፡ የእሳት ፡ የውሃው ፡ አለቃ
ማነው ፡ አዛዥ ፡ የጸሀይዋ ፡ ማነው ፡ አዛዥ ፡ የጨረቃ
ማነው ፡ የምድርን ፡ ዳርቻ ፡ በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ያኖረ
ማነ ፡ ፈርዖንን ፡ በዝቅጠት ፡ በውኃ ፡ በታች ፡ ያስቀረ
ማነው ፡ ከፍታን ፡ የሚያዘው ፡ ዝቅታም ፡ የሚያረግድለት
ማነው ፡ ብድራትን ፡ መላሽ ፡ ከቅርብ ፡ ወይም ፡ ከርቀት
እግዚአብሔር (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
አንተ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክብር (፫x)
አለቆች ፡ የምድር ፡ ፈርጆች ፡ ጐልማሶች ፡ ቆነጃጅቶች
እሳትና ፡ በረዶ ፡ አመዳይ ፡ ጨምሮም ፡ ውርጮች
ተራሮችና ፡ ኮረብቶች ፡ ፍሬ ፡ የሚያፈሩ ፡ ዝግቦች
በቃሉ ፡ ሲንቀጠቀጡ ፡ እዩት ፡ ሲያደንቁት ፡ ፍጥረቶች
ማነው ፡ የዋሁን ፡ ታዳጊ ፡ መመኪያ ፡ ለቅዱሳኑ
ማነው ፡ ቅን ፡ ፈራጅ ፡ መጠጊያ ፡ ለሥሙ ፡ ታምነው ፡ ለጸኑ
ማነው፡ ጉሙን ፡ የሚበትን ፡ የአንበሳን ፡ መንጋጋ ፡ ያደቀቀ
ማነው ፡ ወጥመድን ፡ ሰባሪ ፡ ህዝቡን ፡ ከግዞት ፡ የጠበቀ
እግዚአብሔር (፬x)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር
አንተ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክብር (፫x)

የአምልኮ ፡ ነጻነት (Yeamleko Netsanet)

የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት
በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት
ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት
አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት
ለአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ሱባኤ ፡ ተገብቶ
መሰደድም ፡ ቀረ ፡ ከላይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶ
መግቢያ ፡ በሩ ፡ ሰፋ ፡ ሰው ፡ ተግተለተለ
እንክርዳዱ ፡ ስንዴ ፡ ተኩላው ፡ በግ ፡ መሰለ
የድል ፡ አጥቢያ ፡ አርበኛ ፡ ዘለቀ ፡ ሆ ፡ ብሎ
ውጪያዊ ፡ ምስሉን ፡ ወጉን ፡ አስተካክሎ
በየጓዳው ፡ ፈላ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሰሪ
ራሱ ፡ ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ባለሚኒስትሪ
ዶክትሪኑ ፡ በዛ ፡ መድረክ ፡ ጠበበ
ጥራት ፡ ሳይሆን ፡ ብዛት ፡ ስንቱን ፡ ሰበሰበ
ግርግር ፡ እንዳይሉት ፡ ወይ ፡ ዘመነ ፡ ጥፉ
የአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ብለውት ፡ አረፉ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ
የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት
በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት
ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት
አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት
መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ኮሌጅ ፡ አጠናቅቄያለሁ
ምስክር ፡ ወረቀት ፡ ቆቤንም ፡ ጭኛለሁ
አንግዲህ ፡ የቀረኝ ፡ ሀያ ፡ ሰው ፡ ሰብስቤ
ኪሳቸው ፡ ኪሴ ፡ ነው ፡ ለወጭ ፡ ለቀለቤ
እያሉ ፡ የሚያልሙ ፡ ወንጌል ፡ ተጡዋሪዎች
ዙሪያችን ፡ ፈልተዋል ፡ ሥራ ፡ ጠላቱዎች (፪x)
ቀላዋጮች ፡ ብዙ ፡ ተንባዮች ፡ ለእንጐቻ
መረቅ ፡ ላጠጣቸው ፡ ላበላቸው ፡ ብቻ
እንደ ፡ መተተኛ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ እያሉ
ቅልጥም ፡ ላገኙበት ፡ ይተነብያሉ
የነጻነት ፡ ውልዶች ፡ ስንቱን ፡ ያሞኛሉ
በግርግር ፡ መጥተው ፡ የተቀላቀሉ ፡ የተቀላቀሉ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ
የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት
በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት
ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት
የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት
አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት
ራሱን ፡ የሚያዳንቅ ፡ አገልጋይ ፡ሞልቶናል
ሥሙን ፡ ሲያስተዋውቅ ፡ ፎቶውን ፡ አይተናል
ስብከቴ ፡ ነክቶአቸው ፡ እልፍ ፡ ሰዎች ፡ ዳኑ
አጋንንቶች ፡ ወጡ ፡ ብሎ ፡ ማጋነኑ
ራሱ ፡ እንዳደረገው ፡ በኃይል ፡ በጥበቡ
እውቁልኝ ፡ ብሎ ፡ ሥሙን ፡ ማነብነቡ (፪x)
ባለድርጂቱስ ፡ በጐ ፡ አድራጊ ፡ መሳይ
በሙት ፡ ልጆች ፡ ነጋጅ ፡ ጫና ፡ ጫንቃቸው ፡ ላይ
በድሀ ፡ ሥም ፡ ዞሮ ፡ ባከማቸው ፡ ሁሉ
ፎቁን ፡ ገንብቶበት ፡ የሚታይ ፡ ለሁሉ
ምናልባት ፡ ሲተርፈው ፡ ከርሱን ፡ ካጠገበ
ትርፍራፊው ፡ ሲቀር ፡ ድሆቹን ፡ አሰበ
ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት
ነጻነት ፡ እያሉ
ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)
ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ
ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)

ጊዜው (Giziew)


አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ
ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ
ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ
እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ
ርዕስ ፡ ዜናዎች ፡ ብሎ ፡ እንደጀመረ
ፍርሃት ፡ ፍርሃት ፡ አለኝ ፡ ልቤ ፡ ተሸበረ
ያው ፡ እንደጠበቅኩት ፡ መልካም ፡ ወሬ ፡ የለም
የለቅሶ ፡ የሃዘን ፡ የስብራት ፡ የደም
ጊዜው ፡ ጊዜው ፡ ጊዜው (፪x)
የጊዜው ፡ ምልክት ፡ ወቅቱና ፡ ዘመኑ
የሬዲዮ ፡ ዜና ፡ የማታው ፡ የቀኑ
ያየነው ፡ በቲቪ ፡ የጋዜጣው ፡ ወሬ
መልካም ፡ ቀን ፡ ተወልዷል ፡ ከትናንቱ ፡ ዛሬ
ዋ ፡ ጊዜው ፡ ኦሆሆ ፡ ጊዜው
ስንቱን ፡ አሳየን ፡ ጊዜው
መስከረም ፡ አስራ ፡ አንድ ፡ ገና ፡ በማለዳ
አይሮፕላን ፡ ጥሶ ፡ የህንጻ ፡ ግድግዳ
በፍራቻ ፡ ሆነው ፡ አእላፍ ፡ እያዩ
መንትዮቹ ፡ ህንጻዎች ፡ ፈራረሱ ፡ ጋዩ
ልጆቹዋን፡ እባሕር ፡ ያሰጠመች ፡ እናት
ጭካኔቅ ፡ ግፍዋ ፡ ሲተረክ ፡ በጠዋት
ትምህርት ፡ ቤት ፡ ሰለተጋደሉት
ዜናው ፡ ሲያነበንብ ፡ በአንክሮት ፡ ሰማሁት
አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ
ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ
ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ
እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ
የሩዋንዳው ፡ እልቂት ፡ በሺ ፡ ዘጠና ፡ አራት
በሰነበት ፡ ቂም ፡ በዘር ፡ ቁርሾ ፡ ማክንያት
የዳርፉር ፡ እናቶች ፡ ዛሬም ፡ ደጅ ፡ ናቸው
የበረሃ ፡ አቡዋራ ፡ እየገረፋቸው
ፍልስጤም ፡ ከእስሬኤል ፡ ዛሬም ፡ እልታረቀ
በመካከለኛው ፡ ምስራቅ ፡ ዛሬም ፡ ስንቱ ፡ አለቀ
የሰው ፡ ፈንጂ ፡ ሆኖዋል ፡ ምድርን ፡ ያስጨንቃት
ራሱ ፡ እንደጡዋፍ ፡ ነዶ ፡ አጥፍቶ ፡ ለማጥፋት
አዝ፦ ከእንቅልፌ ፡ ነቅቸ ፡ ዓይኔን ፡ እንደገለጥኩ
ዓለም ፡ እንዴት ፡ ብዬ ፡ ራሴን ፡ ጠየቅሁ
ዘገባው ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ደግሞ ፡ የሚጠብቀኝ
እስቲ ፡ ዜና ፡ ላዳምጥ ፡ ትንሽ ፡ ሬዲዮ ፡ አለኝ
የጦርነት ፡ የሁካታ ፡ ወሬ ፡ በዝቶ
ዝናብ ፡ ጠፍቶ ፡ ምድር ፡ ደርቃ ፡ ችጋር ፡ ገብቶ
ልጅ ፡ ከወለደች ፡ ባል ፡ ከሚስቱ ፡ ተከዳድቶ
ገንዘብ ፡ ነግሶ ፡ መተማመን ፡ ከምድር ፡ ጠፍቶ
ይህ ፡ ጊዜያዊ ፡ መኖርያችን ፡ ተውሳክ ፡ ቦታ
ማብቂያው ፡ ቀርቧል ፡ ሊገለጥ ፡ ነው ፡ የድል ፡ ጌታ
የምናየው ፡ የምንሰማው ፡ ይቀስቅሰን
እንዘጋጅ ፡ ለምጽአቱ ፡ ለታላቅ ፡ ቀን

ተለይተው ፡ ከእኛ (Teleyetew Kegna)


አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከእኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ሰውማ ፡ ዛሬም ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ይላል
አደባባዩስ ፡ መቼ ፡ ይጐላል
ጨዋ ፡ ህዝብ ፡ ፈገግታ ፡ ያሳያል
ልቡ ፡ ግን ፡ በሃዘን ፡ ይጋያል

ወንድ ፡ ሴት ፡ ልጆቹን ፡ ያጣ ፡ ሰው
እህቱን ፡ ወንድሙን ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወላጆቹን ፡ በሞት ፡ ያጣ ፡ ሰው
ያጽናኝ ፡ ያለህ ፡ ይላል ፡ ሆዱን ፡ እየባሰው

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ባልንጀር ፡ አብሮ ፡ አደጉን ፡ ያጣ
የሥራ ፡ ባልደራባዉን ፡ ያጣ
ጐረቤት ፡ ጠያቂውን ፡ ያጣ
የሚያጽናናው ፡ ዛሬ ፡ ከየት ፡ ይምጣ

ሞት ፡ ያልበዘበዘው ፡ ማን ፡ አለ
ቤት ፡ ጓዳው ፡ ያልተመሰቃቀለ
ተርታውን ፡ ከደጃፍ ፡ እደጃፍ
ነጣቂው ፡ ነጠቀ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ ሳያልፍ

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ህጻናት ፡ ተጣለ ፡ ባዶ ፡ ቤት
እናት ፡ አባት ፡ አልቀው ፡ በቅጽበት
ሽማግሌዎች ፡ ጡዋሪም ፡ የላቸው
ተቀጭተው ፡ ተስፋ ፡ ልጆቻቸው

የፍራቻ ፡ ጥላ ፡ የሥጋት
ሰንብቶአል ፡ ምድሪቱን ፡ ከዋጣት
ጠዋት ፡ ያዩት ፡ በሕይወት ፡ ለማታ
በነበር ፡ ይወሳል ፡ በቅጽበት ፡ በአንዳፍታ

አዝ፦ ከሰፈር ፡ ሰፈር
ውጭ ፡ ጉዋሮው ፡ ሳየቀር
ከበራፍ ፡ በራፍ
ከቶ ፡ አንድም ፡ ቤት ፡ ሳታልፍ
አጽናኝ ፡ መንፈስ ፡ ሆይ ፡ ፈጥነህ ፡ ድረስ ፡ ለእኛ
የምንወዳቸው ፡ ተለይተው ፡ ከኛ
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ሆነን ፡ ሃዘንተኛ

ምናልባት ፡ ብትራራ ፡ ጌታችን
የእንጨት ፡ ርብራብ ፡ ሆኗአል ፡ ቤታችን
አሳር ፡ ነው ፡ ዞሮም ፡ መግባቱ
አባዜው ፡ ክፍ ፡ ሆኖ ፡ የቤቱ

ያልፋል ፡ ይህ ፡ የከፍ ፡ ቀን
እግዚአብሔር ፡ በምረት ፡ ሲያውቀን
ስብራት ፡ ይጠገንና
የዓይናችን ፡ እንባ ፡ ፍፁም ፡ ይደርቅና
የትናንት ፡ ወሬ ፡ ይሆንና
ይሞላል ፡ ሰው ፡ በምሥጋና

ይነጫነጭ ፡ ጠላት (Yenechanech Telat)


ፀሐይ ፡ ፈነጠቀች ፡ ደረሰ ፡ ጠዋቱ
ድምጼም ፡ ያስተጋባ ፡ የገደል ፡ ማሚቱ
እግዚአብሔርን ፡ ልጥራ ፡ በውዳሴ ፡ አሃዱ
ይነጫነጭ ፡ ጠላት ፡ ያው ፡ እንደልማዱ (፫x)

ተመቻችቶ ፡ ነበር ፡ እርስቱን ፡ አስፍቶ
ዝምታዬ ፡ ጣፍጦት ፡ ሲቧርቅ ፡ ሰንብቶ
ስለቴ ፡ ደርሶልኝ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ብዘምር
ሽብር ፡ ተፈጠረ ፡ በዲያብሎስ ፡ ቅጥር

በማለዳ ፡ ዜማ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከበረ
ክፋት ፡ ሸራቢው ፡ ግን ፡ ዲያብሎስ ፡ አፈረ
እርሱ ፡ እንዳሻው ፡ ይሁን ፡ የሲኦሉ ፡ ሲሳይ
እኔ ፡ ግን ፡ ልዘምር ፡ ላለው ፡ ዙፋኑ ፡ ላይ

በክረምት ፡ በበጋ ፡ በህመም ፡ በጤና
በክብር ፡ በውርደት ፡ በድል ፡ እንደገና
በማግኘት ፡ በማጣት ፡ በትርፍ ፡ በኪሳራ
ስንቱን ፡ አቋርጠናል ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ

ዙሬያየን ፡ የማየው ፡ እልልም ፡ ባያሰኝ
የክብሩን ፡ መስዋእት ፡ ልነፍግ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ
በዘመነ ፡ መልካም ፡ ወይ ፡ ዘመን ፡ ቁዛሜ
እወድሰዋለሁ ፡ በሰዎች ፡ ፊት ፡ ቆሜ

በቃላቶች ፡ ውበት ፡ ጤም ፡ ባለው ፡ ዜማ
ተነሱ ፡ እንወድስ ፡ ድምጻችን ፡ ይሰማ ፡
የልባችን ፡ ክብደት ፡ አስጨናቂው ፡ ሁሉ
እንደ ፡ እያሪኮ ፡ ግንብ ፡ ይናዳል ፡ ከውሉ

ጆሯችንን ፡ ሰርቆ ፡ ሹክ ፡ የሚለን ፡ ጠላት
ሰፍሮ ፡ ትከሻችን ፡ ሲጭንብን ፡ መዓት
ማርከሻው ፡ መዝሙር ፡ ነው ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና
ጥንትም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ መች ፡ ይበገርና

መርምር ፡ ሩጫዬን (Mermer Ruchayien))


የቆምኩበት ፡ ስፍራ ፡ ይህ ፡ ግዑዙ ፡ መሬት
የሰላም ፡ ነው ፡ የደም ፡ ጠብ ፡ የበቀለበት
የእርምጃዬ ፡ ማብቂያ ፡ የእግሮቸን ፡ አቅጣጫ
መርምር ፡ ሩጫዬን ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ

ልቤን ፡ ብትከፍተው ፡ ጫካኝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ገራም
የእጆቸ ፡ መዘርጋት ፡ ለሰይፍ ፡ ነው ፡ ለሰላም
ሌሊት ፡ በምንጣፌ ፡ በጭርታው ፡ ሰዓት
የማውጠነጥነው ፡ የአዕምሮዬ ፡ ሙላት

ከአንተ ፡ ምን ፡ ይደበቃል
ፍጥረት ፡ እርቃኑን ፡ ነው ፡ ግልጥልጥ ፡ ብሏል

ድልድል ፡ ቢሆን ፡ ገደላማ
ብራ ፡ ቡሆን ፡ ወይ ፡ ደመናማ
እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ
ደረቅ ፡ መሬት ፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ
በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ
የሚያልፍ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ
ዓይኖቼ ፡ ተከፍተው ፡ ወዴት ፡ አማተሩ
የምላሴ ፡ ቅምሻ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ መራሩ
ቃሌ ፡ የአንደበቴ ፡ የሚወረወረው
ለጐረቤት ፡ ጆሮ ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው

ከአንተ ፡ ምን ፡ የደበቃል
ድልድል ፡ ቢሆን ፡ ገደላማ
ብራ ፡ ቡሆን ፡ ወይ ፡ ደመናማ
እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ
ደረቅ ፡ መሬት ፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ
በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ
የሚያልፍ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ

የዛሬ ፡ ቤተክርስቲያን (Yezarie Bietekerestiyan)


በቀድሞው ፡ ስብስብ ፡ በአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት
ምዕመናን ፡ አብረው ፡ በተከማቹበት
ንብረቱን ፡ ገንዘቡን ፡ ሁሉን ፡ እያመጣ
ማንም ፡ ሳይራቆት ፡ እንጀራም ፡ ሳያጣ
በአንድ ፡ ልብ ፡ ጌታን ፡ እያመሰገኑ
ይቆርሱ ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ ምዕመኑ
ህብረት ፡ እንድናደርግ ፡ ያስተማረን ፡ ቃሉ
እንዲህ ፡ ዓይነት ፡ ነበር ፡ ምዕመን ፡ አስተውሉ
ዛሬ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ እያሉ ፡ የሚጠሩት
በየጐዳናው ፡ ላይ ፡ አስጊጠው ፡ የሰሩት
አናጢ ፡ የዋለበት ፡ ከመሰረት ፡ ከላይ
በቁመት ፡ በስፋት ፡ ባሻገር ፡ የሚታይ
ለዓይን ፡ ጥጋብ ፡ እንጂ ፡ ሕይወት ፡ የሌለበት
ያዘነ ፡ የራበው ፡ ደጅ ፡ የሚቆምበት
የነፍሳት ፡ ጥሪ ፡ ስብከቱ ፡ ተረስቶ
እቁብ ፡ መሰብሰቢያ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ ቤት ፡ መጥቶ

የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ ህብረት ፡ የሃዋሪያቱ
በአንድ ፡ ልብ ፡ ሁሉም ፡ የቆረሱበቱ
ሁሉም ፡ የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ በልብ ፡ በአንደበቱ
በዚህ ፡ ዘመን ፡ ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁን ፡ በሉ
ያ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጸሎት ፡ ለቅዱሳን ፡ ሁሉ

ሰንበት ፡ ጠብቆ ፡ እንዲያው ፡ ለወጉ
መሰባሰቡ ፡ ደንቡን ፡ ማድረጉ
ያለክርስቶስ ፡ ኦና ፡ ነው ፡ ቤቱ
ጭፈራው ፡ አጉል ፡ ዝማሬው ፡ ከንቱ

የዛሬው ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ባለአስር ፡ ሺህ ፡ አባላት
የቁጥር ፡ እሽቅድምድም ፡ የአባል ፡ ቅጽ ፡ ሙላት
መቶ ፡ የነበረው ፡ በሺህ ፡ እንዲቆጠር
ማን ፡ ይበልጥ ፡ በብዛት ፡ ብሎ ፡ መፎካከር
ህዝቡ ፡ ተጠራቅሞ ፡ አዳራሽ ፡ ይጠባል
ሰው ፡ ሰውን ፡ አያውቀው ፡ ይገባል ፡ ይወጣል
የዛሬው ፡ እረኛ ፡ አባላት ፡ ይቆጠራል
ለጋስና ፡ ሃብታሙን ፡ ለማግኘት ፡ ይጥራል

የሥም ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሞልቷል ፡ በየጓሮው
ገብተው ፡ ለሚያዩት ፡ ግን ፡ ውስጡ ፡ ግን ፡ ሌላ ፡ ነው
መሪዎች ፡ ተብለው ፡ የሚያስተዳድሩ
እንደ ፡ ጳውሎስ ፡ መስራት ፡ ሰንፈው ፡ ያልተማሩ
ሰርተው ፡ የማያውቁ ፡ ወንበር ፡ የሚያሞቁ
በላብ ፡ የማግኘትን ፡ ሚስጥር ፡ የማያውቁ
በስልጣን ፡ በገንዘብ ፡ እርስ ፡ በርስ ፡ ጡጫ
እግዚአብሔር ፡ በእነርሱ ፡ የዓለም ፡ ማላገጫ

በየእሁዱ ፡ ጉባኤው ፡ ስጡ ፡ ስጡ ፡ ሰፍኖ
ከሃብታም ፡ ከደሃው ፡ ብር ፡ ተለምኖ
ቀድሞ ፡ ከተሰሩት ፡ አብልጥ ፡ የሚያኮራ
ባልሚሊዮን ፡ ብር ፡ አዳራሽ ፡ ሊሰራ
የእገሌ ፡ ቤተክርስቴን ፡ እጹብ ፡ ድንቅ ፡ ስራ
የሰው ፡ ልጅ ፡ የራሱን ፡ ስሙን ፡ እንዲያስጠራ
ባዶ ፡ ሆድ ፡ የመጡ ፡ የራባቸው ፡ ሁሉ
ለአዳራሹ ፡ መስሪያ ፡ ስጡ ፡ ይባላሉ

በሰንበቱ ፡ ህብረት ፡ ግራ ፡ ቀኝ ፡ ላየ ፡ ሰው
አለ ፡ በጌታ ፡ ቤት ፡ ያጣ ፡ የሚቆርሰው
ሱሪው ፡ የተጣፈ ፡ መጫሚያው ፡ ያለቀ
መቆም ፡ የተሳነው ፡ አቅሙ ፡ የደቀቀ
ሞልቷል ፡ ውስጡ ፡ የሚጮህ ፡ በጌታ ፡ ፊት ፡ ወድቆ
የእግዚአብሔር ፡ ገንዘብ ፡ ግን ፡ ባንክ ፡ ተጨናንቆ
ስስታም ፡ መሪዎች ፡ ያው ፡ ሲስገበገቡ
የመንግስት ፡ ሲሳይ ፡ አይቀርም ፡ መሆኑ

በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ በረከት ፡ ይብዛ
መብል ፡ ይሁን ፡ ለራበው ፡ በዛ
የሳጥኑን ፡ ቁልፍ ፡ የያዛችሁ
የጌታን ፡ ገንዘብ ፡ ጉዋዳ ፡ ያሸሻችሁ
ሰማይ ፡ ጫፍ ፡ ደርሶዋል ፡ መሰሰታችሁ
ለራበው ፡ ለጠማው ፡ በትኑት ፡ አውጡና
የእግዚአብሔርን ፡ ገንዘብ ፡ ማካበት ፡ ይቅርና

የሰው ፡ አስታማሚ (Yesew Astamami)


የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ውሱን ፡ ነው ፡ ስልቹ
ይርዳሉ ፡ እጆቹ ፡ ይከብዳሉ ፡ ዓይኖቹ
የሰው ፡ አስታማሚ ፡ ጥቂት ፡ ነው ፡ ትዕግስቱ
ወቅት ፡ የማይወስነው ፡ ጌታ ፡ ማጽናናቱ

በራችሁ ፡ ተዘግቶ ፡ ተረሳን ፡ ያላችሁ
ውኃ ቀና ፡ አድርጐ ፡ ጠፍቶ ፡ የሚያጠጣችሁ
በሩቁም ፡ በቅርቡ ፡ በያላችሁበት
ቁስላችሁ ፡ ይጠግግ ፡ በጌታ ፡ ምህረት

አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን
ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን
እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ
ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ

ማነው ፡ የሚገደው ፡ ለእነኛ ፡ አቅም ፡ ላጡት
ፀሐይ ፡ ለማይሞቁ ፡ ደጅ ፡ ለማይውጡ
ከዓይናችን ፡ ከጠፉ ፡ ፈጥነው ፡ ይረሳሉ
ኩርሲያቸው ፡ ተወስዶ ፡ እያሉ ፡ እንደሌሉ

አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን
ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን
እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ
ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ

ፌጦው ፡ ድንገተኛው ፡ ሁሉ ፡ ተሞክሮ
ሃኪሙም ፡ ሳይታክት ፡ በጥበብ ፡ በአይምሮ
በሩቅ ፡ በጐረቤት ፡ ተመክሮ ፡ ተዘክሮ
እልፍ ፡ አልተገኘም ፡ ተጥሮ ፡ ተግሮ

በህክምና ፡ ሂደት ፡ መድኃኒት ፡ ቅመማ
በሳይንስ ፡ ጥናት ፡ በሊቆች ፡ ግምገማ
የዕድሜያችሁ ፡ መጽሃፍ ፡ ተከድኗል ፡ ያሉአችሁ
ወደ ፡ ተዓምር ፡ ጌታ ፡ ይመልከት ፡ ዓይናችሁ

አዝ፦ ከአጥር ፡ ውዲህ ፡ ተከማችተን
ጭፍራ ፡ ዝላዩን ፡ ትተን
እስቲ ፡ እንውጣ ፡ ከአዳራሹ
ፍቅር ፡ ድጋፍ ፡ ወደሚሹ

ህመማችሁ ፡ ጸንቶ ፡ ቀና ፡ የማትሉት
ፋታ ፡ የማይሰጣችሁ ፡ ውጋት ፡ ቀርጥማቱ
ውሉ ፡ የጠፋችሁ ፡ የቀን ፡ የሌሊቱ
ጌታ ፡ ይዳብሳችሁ ፡ ባላችሁበቱ

በበሽታ ፡ አቅም ፡ የለ
ሥጋ ፡ አጥንትህ ፡ የሰለለ
በፍራቻ ፡ ባሕር ፡ ስምጠት
ሰውም ፡ ከቦህ ፡ ብቸኝነት
ከሃኪሙ ፡ ተስፋ ፡ አጥተሃል
ጤና ፡ አዳሙም ፡ ሰልችቶሃል
እዛው ፡ ባልጋው ፡ ባለህበት
ፈዋሹ ፡ አምላክ ፡ ይንካህ ፡ ድንገት

ምህረት ፡ አልወረደም (Meheret Alweredem)


እየመሽ ፡ ነጋ ፡ እየነጋም ፡ መሽ
ዛሬም ፡ ጉስቁልና ፡ ከምድሪቱ ፡ እልሸሸ
የነገዋ ፡ ፀሐይ ፡ ሙቀት ፡ ይዛ ፡ ትምጣ
የሃገር ፡ ልጅ ፡ በርዶታል ፡ ድሪቶም ፡ ስላጣ

ከትናንት ፡ ዛሬ ፡ ይሻል ፡ ይሆን ፡ ብለን
የበጐ ፡ ቀን ፡ ያለህ ፡ አልመጣም ፡ ጠብቀን
በደረቀ ፡ ላንቃ ፡ ውኃ ፡ እያረረበት
አየን ፡ በአደባባይ ፡ ፍጥረት ፡ ሲንከራተት

ገና ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ አልወረደም
የሃገሬ ፡ ንዳድ ፡ ዛሬም ፡ አልበረደም
ገና ፡ ነው ፡ ቁጣው ፡ መቸ ፡ ሰከነ
በሽታና ፡ ርሃብ ፡ በሃደሬ ፡ ገነነ

በረሃብ ፡ ጉስቁልና ፡ በጥማት ፡ ተቃጥሎ
በብርድ ፡ ተጠብሶ ፡ በፀሐይ ፡ ከሳስሎ
ኑሮ ፡ እንደሬት ፡ መሮት ፡ ለሞቱ ፡ የሚጐመጅ
በጐዳናው ፡ ከፈፍ ፡ ተዘርግቷል ፡ እድጅ

እየመሽ ፡ ነጋ ፡ እየነጋም ፡ መሽ
ዛሬም ፡ ጉስቁልና ፡ ከምድሪቱ ፡ እልሸሸ
የነገዋ ፡ ፀሐይ ፡ ሙቀት ፡ ይዛ ፡ ትምጣ
የሃገር ፡ ልጅ ፡ በርዶታል ፡ ድሪቶም ፡ ስላጣ

ማረን ፡ ጌታችን ፡ ፈጽመህ ፡ አትቅጣን
ጠበልክን ፡ እርጨን ፡ ጠምቶናል ፡ አጠጣን
ታማሚው ፡ ይፈወስ ፡ የራበው ፡ ሰው ፡ ይጥገብ
የፍርድ ፡ አዋጅ ፡ በቅቶ ፡ ምህረቱ ፡ ይነበብ

ክራራይሶ (፪x) ፡ እግዚኦ ፡ ማሃረነ ፡ ክርስቶስ (፪x)

ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ (Tamagn Sew Tefa)


ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ
ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ
ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ
በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ
ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ

በእርጅናዬ ፡ ዘመን ፡ አንድ ፡ እውነት ፡ አገኘሁ
አደራ ፡ ማይበላ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው
ብዙ ፡ ወሰደብኝ ፡ ሚስጢሩ ፡ ሳይገባኝ
ይሄ ፡ ሰው ፡ ማመኔ ፡ ደህና ፡ አድርጐ ፡ ጐዳኝ

የዘመናት ፡ ጥቅልል ፡ የምድር ፡ እና ፡ ሰማይ
የጌታን ፡ መመለስ ፡ በሁለት ፡ ዐይኖቸ ፡ ላይ
ያወኩት ፡ ዛሬ ፡ ስአቱ ፡ መድረሱን
ያበላሁት ፡ ወዳጂ ፡ ሲያፋጭብኝ ፡ ጥርሱን

ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል
ጨዋነትና ፡ ክበር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት
የቃል ፡ አምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት

ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በአገሩ
ታማኝ ፡ ሰው ፡ ጠፋ ፡ በምድሩ
ሰዎች ፡ አላገኙም ፡ ቢዞሩ ፡ ቢዞሩ
በፈረሥም ፡ ጠፋ ፡ እንኳንስ ፡ ሰው ፡ በእግሩ
ታማኝ ፡ ግን ፡ በሰማይ ፡ አለ ፡ በመንበሩ

እወየው ፡ ጯዋነት ፡ ሰፈር ፡ ጥሎ ፡ ሄዷል
ወገን ፡ በወገኑ ፡ ያልፍርሃት ፡ ነግዷል
ያስቀመጡት ፡ እቃ ፡ አይገኝም ፡ ዳግም
ሁሉ ፡ ቃል ፡ አጥፊ ፡ መሃላ ፡ ቢያደርግም

ወንድሞቹ ፡ ሸጡት ፡ ዮሴፍን ፡ ለእንጀራ
ማዕድ ፡ የተጋሩት ፡ ሆኑት ፡ ባላጋራ
የጥንት ፡ ታሪክ ፡ ነው ፡ ዛሬ ፡ በዚህ ፡ የለም
ብዬ ፡ ነበር ፡ ኋላ ፡ በራሴ ፡ ሊፈጸም

ዘመን ፡ ተለዋውጧል (፪x)
በኩርናን ፡ በእንጐቻ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ለውጧል
ጨዋነትና ፡ ክብር ፡ ውህ ፡ ፈሰሰበት
የቃል ፡ እምነት ፡ ቀርቷል ፡ ፊርማ ፡ ከሌለበት

እግዚአብሔር ፡ የታለ ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ (Egziabhier Yetale Lemen Telegnaleh


እግዚአብሔር ፡ የታለ ፡ ለምን ፡ ትለኛለህ
ፍጥረታት ፡ በዙሪያህ ፡ ከበውህ ፡ እያየህ
ዓይን ፡ አጥርቶ ፡ ቢያይ ፡ ጆሮችህ ፡ ቢያቀኑ
የእርሱን ፡ ህልውና ፡ ታይ ፡ ነበር ፡ በውኑ

ውጣ ፡ ወደ ፡ ሜዳው ፡ ሂድ ፡ ወደ ፡ ሃይቁ
የፍጥረትን ፡ ሰሪ ፡ ቢያሻህ ፡ መጠየቁ
አቀበቱን ፡ ውጣ ፡ ቁልቁለቱን ፡ ውረድ
ሜዳ ፡ ለጥ ፡ ያለውን ፡ ወይ ፡ ረዥሙን ፡ መንገድ
በደረስክበቱ ፡ የሰማህ ፡ ያየው
ሰሪና ፡ ተካዩ ፡ ሕያው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

እያት ፡ ቢራቢሮ ፡ ተፈጥሮ ፡ ያስጌጣት
ክንፎቹዋ ፡ ርግብግብ ፡ ውበት ፡ የተሰጣት
ተመልከት ፡ ወፊቱን ፡ ጐጆ ፡ ስትራ
መሰረቱን ፡ ጥላ ፡ ለፍታ ፡ ጥራ ፡ ግራ
የትም ፡ ዞራ ፡ ዞራ ፡ በአየር ፡ በደመና
ተመልሳ ፡ ቤቷ ፡ ሳትስት ፡ ጐዳና

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ
የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ
ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ
ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ

ነፋሱም ፡ ያፏጫል ፡ ዛፉም ፡ ይራወጣል
ጂረቱም ፡ ይፈሳል ፡ ምንጩም ፡ ያው ፡ ይፈልቃል
ቀን ፡ ለፀሐይ ፡ መውጫ ፡ ማታው ፡ ለጨረቃ
ጨለማና ፡ ብርሃን ፡ በተራ ፡ ጥበቃ
ወቅት ፡ ሲፈራረቅ ፡ ዛሬም ፡ እንደጥንቱ
እግዚአብሔር ፡ ያውልህ ፡ እየው ፡ በፍጥረቱ

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ
የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ
ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ
ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ

ከፀሐይ ፡ ባሻገር ፡ ብዙ ፡ ዘመን ፡ ርቀት
እልፍ ፡ አእላፍ ፡ ክዋክብት ፡ ያሸበረቀበት
ዓሣ ፡ ነባሪውም ፡ በውቂያኖስ ፡ ጥልቀት
አናብስቱ ፡ በዱር ፡ ሲያገሱ ፡ በርቀት
ገብረ ፡ ጉንዳን ፡ ሰልፉ ፡ ሁከት ፡ የሌለበት
ውብ ፡ ፍጥረት ፡ ዙሪያህን ፡ አልመጣ ፡ እንደድንገት

አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ በእጅህ ፡ ቢያሻህ ፡ ለመዳሰስ
የልብህን ፡ ጥያቄ ፡ ምናልባት ፡ ቢመለስ
ተመልከት ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራውን ፡ በእጁ
ወጥተህ ፡ ወደ ፡ ደጁ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ