የእግዚአብሔር ጣት ( Finger of GOD )

2 Column CSS Layout - concise design
የእግዚአብሔር ጣት (Finger of God) ይህ ገጽ በዋናነት በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ቁጥር 20 ላይ የተመሰረቱ ትምህርቶች የሚተላለፍበት አምድ ነው፡፡

“እኔ ግን በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች፡፡” የሉቃስ ወንጌል 11፡20
በሁለተኛ ደረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ተጠቅሶ የምናገኘው በተመሳሳይ በዚሁ የዘጸአት መጽሐፍ ውስጥ በምዕራፍ 31 ቁጥር 18 ላይ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ይህ ቃል በመንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው በብሉይ ኪዳን በዘዳግም ምዕራፍ 9 ቁጥር 10 ላይ እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ በአራተኛ ደረጃ እና በመጨረሻ ይህ ቃል በእግዚአብሔር ወልድ በጌታ ኢየሱስ አንደበት ከላይ በተፃፈው በሉቃስ ወንጌል መጽሐፍ ውስጥ እንደተናገረ ተጽፎ ይገኛል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የእግዚአብሔር ጣት በእንግሊዝኛው ፍቺ “Finger of God” አሊያም ቃሉ መጀመሪያ በተፃፈበት ዕብራይስጥ ፍቺ “ዳክቲሎስ” በሚል ተጽፎ የምናገኘው በዘጸአት መጽሐፍ በምዕራፍ 8:19 ላይ ባለው ክፍል ውስጥ ነው፡፡ በዚህ መግቢያ ገጽ ላይ እንድናየው የፈለግነው የእግዚአብሔር ጣት በሚል በመንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰበት ቦታ እና ብዛት ላይ ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ቃል ላይ ተመስርተው የተላለፉ መልዕክቶችን በቀጣይ በተከታታይ ትምህርቶች በትንታኔ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ