አልበም ፯

Album 7

አልተማረም አሉኝ


የማመልከዉ አምላክ ሳይንስ አይጨብጠዉ
የእልፍ ቃላት ብዛት እዉቀት አይገምተዉ
መንፈሳዊ አይኖች ተከፍተዉ ካላዩት
ቃሉ ሞኝነት ነዉ አዉቀናል ለሚሉት
ሞኝ ነዉ አልተማረም አሉኝ
ለእግዚአብሄር አድሬለት ቢያዩኝ
ትርፌንና ጥቅሜን ባለማወቃቸዉ
እኔ አዘንኩላቸዉ
ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያዉ ሳይቆለፍ
የሰዉ ልጅ ይመለስ
ለሚጠፋዉ ዓለም ጉልበቱን ከማፍሰስ
የሚጠፋ ጥሪት ማከማቸት ትቼ
ዘላለማዊዉን ለማግኘት ተግቼ
ጌታዬን የሙጥኝ ብዬ በወሰኔ
ከአዋቂዎች በላይ አልሆንኩም ወይ እኔ

አዝ...
ምድርና ሰማይን ያበጀዉ ፈጣሪ
አይመረመርም ገብቶ ላብራቶሪ
ቁጥርን ከቁጥር ጋር ሲያጋጩ ቢኖሩ
አያዩትም ጌታን እሩቅ ነዉ ሐገሩ

አዝ...
ሠዓቱ ገና አለ ጊዜአችን አልገፋም
እግዚአብሄር ደጁን በሰዉ ልጅ አልዘጋም
ከማንቀላፋቱ ነቅቶ ለታረመ
ብርሃን ነዉ ገና ዛሬ መች ጨለመ
አዝ...

ከትንሽነቴ ሠልፍ ይበዛብኛል

ከትንሽነቴ ሠልፍ ይበዛብኛል
እንቅፋቱ በዝቶ ያቆሣሥለኛል
እፎይ የምልበት የእረፍቴ ሠዓት
ላይኔ አይታየኝም ለአእላፍ ቀናት#2

ጌታ ሆይ...

ምክንያቱን አላዉቅም መሥቀሌ ብዙ ነዉ
ትከሻዬን አሥፋዉ ችዬ እንድሸከመዉ
በግፈኞችም እጅ ወድቄ አቅሻለሁ
መንገዴን አጥብበዉ ብዙ ታግያለሁ
ሥጋዬ በህመም ደክሞ ተንጋልዬ
ቀናት ተፈራርቀዉ ሣለሁኝ ባልጋዬ#2

አዝ...

በቃልህ ከሆነ ሀሞት እቀምሣለሁ
የሚያሥችል ሃይልህን እከናነባለሁ
የማታ የማታ ባለድል እሆናለሁ
የፀና ሥምህን በእምነት
እጠራለሁ#2

አዝ....

ሠገነት ላይ በቅሎ እንደደረቀ ሣር
ፈታኜ ይጠዉልግ ይገፍተር ወደ ዳር
ብሩህ ቀን የደሥታ አዲሥ ቀን አያለሁ
አንተን ተደግፌ ድሌን አዉጃለሁ#2

አዝ...

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ