ድንቅ ፡ ሥራ (Denq Sera)
ኮረብታውን ፡ ወጥቼ ፡ እፎይ ፡ አልኩኝ
ድንቅ ፡ የሆኑ ፡ ፍጥረታትን ፡ እያየሁኝ
ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ ለማለት ፡ አልደፈርኩም
በዙሪያዬ ፡ አጫዋች ፡ አላጣሁም
አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ቀስ ፡ እያልኩኝ ፡ ቀጠልኩኝ ፡ እርምጃዬን
አቤት ፡ ወፎች ፡ ከበውኛል ፡ ዙሪያዬን
ልዩ ፡ ልዩ ፡ ቀለም ፡ ለብሰው ፡ ሲጫወቱ
ደስ ፡ ያሰኛል ፡ የአምላክ ፡ ጥበብ ፡ መሰረቱ
አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ሽው ፡ እያለ ፡ በሚያዝናናኝ ፡ ነፋስ ፡ ደግሞ
ሲወዛወዝ ፡ የ. (1) . ፡ አንገት ፡ ዘሞ
አንዴ ፡ ቀና ፡ አንዴ ፡ ጐንበስ ፡ አቤት ፡ . (2) .
እንዴት ፡ ሰራው ፡ ታላቅ ፡ ጌታስ ፡ ያሰኛል
አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
የአበቦቹ ፡ መዓዛ ፡ እያወደኝ
ልዩ ፡ ቃና ፡ ለአካላቴ ፡ እየሰጠኝ
በአምላክ ፡ እጆች ፡ በተሰሩት ፡ ተደንቄ
ተመለስኩኝ ፡ ወደ ፡ ቤቴ ፡ ብዙ ፡ አውቄ
አዝ፦ ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
ድንቅ ፡ ስራ ፡ የአምላክ ፡ ስራ ፡ አይወራ
እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ቢሆን (Egziabhier Sewen Bihon)
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ቢሆን
ከቶ ፡ ምን ፡ በዋጠን
ምስኪን ፡ የሚያጽናና ፡ አምላክ ፡ ነውና (፪x)
ወዳጄ ፡ መስሎ ፡ ጠላት
ገብቶ ፡ በደከምኩበት
አቆሰለኝ ፡ አድብቶ
ጥርሱን ፡ አሳይቶ (፪x)
ፊት ፡ አይቶ ፡ አያደላ
አምላክ ፡ የደሃ ፡ ጥላ
ሁሉም ፡ እኩል ፡ ነው ፡ ለእርሱ
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ (፪x)
ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተመስገን
የወደቅን ፡ እኛን ፡ ሰው ፡ አደረከን
የወደቅን ፡ እኛን ፡ ክብር ፡ አለበስከን (፪x)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ