አዳኜ ፡ ኢየሱስ (Adagnie Yesus)
አዝ፦ አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ለቀኝለት
እግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ነፍሴን ፡ አስጨንቛት ፡ የጥላቴ ፡ ጩኸት
አይኖቼን ፡ ባነሳ ፡ ከላይ ፡ ስመለከት
ከመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ እምባዬን ፡ አበሰ
ያሰረኝ ፡ ገመድ ፡ ጌታ ፡ በጣጠሰ
አዝ፦ አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ለቀኝለት
እግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
የሞትቀንበር ፡ ከቦኝ ፡ ያመፅ ፡ ፈሳሽ ፡ ዉጦኝ
ሲኦል ፡ አፉን ፡ ከፍቶ ፡ ባጥንቴ ፡ አስቀርቶኝ
ስሞታ ፡ ነገርኩኝ ፡ ላምላኬ ፡ ሳልሰለች
እግዚአብሔር ፡ ተቆጣ ፡ ምድር ፡ ተናወጠች
አዝ፦ አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ለቀኝለት
እግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ጠላቴን ፡ ሰበረ ፡ እንዳያንሰራራ
ከቁጣው ፡ ጢስ ፡ ወጣ ፡ ከመቅደሱ ፡ በራ
ጠላቴን ፡ ረገጠ ፡ እንደመንገድ ፡ ጭቃ
ነፃነቴን ፡ ሰጠኝ ፡ መቆዘሜ ፡ በቃ
አዝ፦ አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ለቀኝለት
እግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ዛሬማ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ቀስት ፡ እገትራለሁ
በኮረብታ ፡ ሆኜ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ
ፅኑ ፡ እግር ፡ ለሰጠኝ ፡ የማይንሸራተት
ለናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
አዝ፦ አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ለቀኝለት
እግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ