በዚህ ድህረ-ገፅ ከንጉሡ ማዕድ እንበላለን ከዚህ ዓለም ገዥ ከተባለው ንጉሥ ማዕድ አንበላም፡፡ በዚህ ማዕድ የክርስቲያኖችን ኅብረት የሚያጠናክር፣ የጠላትን ህቡዕ አሠራር የሚያጋልጥ፣ የክርስቶስ ወታደሮችን የቃሉን ጦር የሚያስታጥቅ እና የጨለማውን ሥራ የሚያፈርስ ድምፅ ነው፡፡
ይህ የጌታን መንገድ አዘጋጁ የሚል ድምፅ ነው፡፡ አዘጋጅ አይደለም ቃሉ የሚለው አዘጋጁ እንጂ፡፡ ኑ የጌታ ግብዣ ሊሆን የሚገባ ማዕድ ሃሳባችሁን በማካፈል አብራችሁን ታዘጋጁ ዘንድ ተጋብዛችኋል!
ይህ ቃል በዋናነት የተወሰደው ከትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 1 ቁጥር 8 ሲሆን ይኸውም ለንጉሡ አገልጋይ እንዲሆኑ በተመለመሉት አራቱ ወጣት ዕብራውያን ውሳኔ መሠረት ከንጉሡ ማዕድ በመብላት እንዳንረክስ ብለው አለቃቸውን የለመኑበትን ቃል መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ሆኖም የዚህ ድኅረ ገጽ ዋና ስም (ዳክቲሎስ) ጨምሮ በዋናነት ከላይ በተገለጸው የዳንኤል መጽሐፍ ላይ ያተኮረ ሳይሆን በተቃራኒው የነገሥታት ንጉስ የሆነውን የጌታ ኢየሱስ ማዕድ እንድትበሉ ተፈቅዶላችኋል በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ